በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈረመው አልጀርስ ስምምነት 23 ዓመት ሞላው


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት

ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጥፋትን ያስከተለውን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የድንበር ጦርነት ለማስቆም በሁለቱ ሀገራት መካከል የእርቅ ስምምነት ከተፈረመ ዛሬ 23 ዓመት አስቆጠረ።

እለቱን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ "የዛሬ 23 አመት፣ በዛሬዋ እለት፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ የአልጀርሱን ስምምነት በመፈራረም፣ የጋራ ድንበር ለማካለል ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።" ብሏል።

የሚንስትር መስሪያቤቱ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ባወጡት በዚሁ መግለጫ እ.አ.አ በ2018 ሁለቱም ሀገራት በፈፀሙት ታሪካው የሰላም ስምምነትም፣ በአልጀርሱ ስምምነት የተቀመጡትን የድንበር ማካለሎች ለማክበር በድጋሚ ቃል መግባታቸውን አሳታውሰዋል።

"በዚህች ቀን፣ የሁለቱም ሀገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው" ያሉት ሚለር፣ ዩናይትድ ስቴትስ የአልጀርሱን ስምምነት እንደምትደግፍ እና ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በፈጠሩት የሰላም መንፈስ ለበለጠ የተረጋጋ እና የበለፀገ ቀጠና አብረው እንዲሰሩ እንደምታበረታታ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG