በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነት ውስጥ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ድጋፍ እንደማይደረግላቸው ተናገሩ


ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ

የህወሓት ታጣቂዎች ምሥራቃዊ የአማራ ክልልን ተቆጣጠረው በነበሩበት ወቅት “ፆታዊ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል” ለተባሉ ቁጥራቸው ከ500 የሚበልጥ ሴቶች የህክምናና የምክር አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የደሴ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ አስታውቀዋል።

ተጎጂዎቹ ሴቶች ከደረሰባቸው የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት በምክርና በህክምና እያገገሙ መሆናቸውን ተናግረው ኑሯቸውን ለማስቀጠል የሚያስችል ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ቀደም ሲልም ትግራይ ውስጥ ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ወቅትም ተመሳሳይ ጥቃቶች እንደተፈፀሙባቸው የተነገረ ሴቶች በከበደ ችግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

እንዲህ ዓይነት ጥቃቶች በጦርነቶች ወቅት ተደጋግመው ሲፈፀሙ እንደሚታይ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አጥኒ አቶ ፍሰሃ ተክሌ ሰሞኑን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ገልፀው ነበር።

በሌላ በኩል በዚህ ጦርነት ውስጥ በሴቶች ላይ በሁሉም ወገኖች ጥቃቶች ተደጋግመው መፈፀማቸው የሚሰማው ለምን እንደሆነ ሰሞኑን በቪኦኤ የተጠየቁት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አጥኒ አቶ ፍሰሃ ተክሌ መልስ ሰጥተው ነበር።

በጦርነት ውስጥ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ድጋፍ እንደማይደረግላቸው ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:58 0:00

XS
SM
MD
LG