በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራማፎሳ ለአፍሪቃ አገሮች ከቀረጥ ነፃ የሆነ ገበያ የሚያስገኘው ዕድል ዘለቄታ እንዲኖረው ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ የውጪ ንግድ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ ወደ ትልቁ የዓለም ገበያ፡ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የሚፈቅደው ሕግ የሚራዘበት ጊዜ፡ አጭር መሆን ‘መዋዕለ ንዋይ ወጭ ሊደርግ የሚችልባቸውን እድሎች ያደናቅፋል’ ሲሉ በዚሁ በጉዳዩ ትኩረት ላደረገው ጉባኤ በሰጡት አስተያየት አመለከቱ።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2000 ዓም የተጀመረው አጎአ የሥራ ጊዜ በሁለት ዓመታት ውስጥ መስከረም 2025 ላይ ያበቃል። የአገልግሎት ዘመኑ ሊራዘም የሚችልበትን ሁኔታ አመልክቶም ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ጉዳዮች ተወካይ ካትሪን ታይ በዚሁ ጉባኤ ላይ በሰጡት አስተያየት፡ ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ ጋር ለሚደረጉ የንግድ ልውውጦች መጠናከር መልካም ራዕይ ለመቅረጽ የሚያስችል እድል ይኖራል የሚል ዕምነት ይዛ እንደተነሳች አስታውሰዋል።

የአፍሪካ አገሮች በአጎዋ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ስጋት ያደረባቸውን የንግድ ድርጅቶች እና ባለሃብቶች ለማረጋጋት፡ ሕጉ ለውጥ ሳይደረገበት

ለመጭው 10 አመታት ዳግም ፈጥኖ እንዲራዘም የሚል ጥሪያ በማሰማት ላይ ናቸው።

ባለፈው አመት ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ የአፍሪካ የውጪ ንግድ ምርቶች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከቀረጥ ነጻ የገቡበት አጎአ እንዲራዘም የባይደን አስተዳደር እና የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጪዎች በተመሳሳይ የድጋፍ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG