በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረመዳን በዋሽንግተን ዲሲ


ሰላት በፈርስት ሂጂራ መስጊድ
ሰላት በፈርስት ሂጂራ መስጊድ

መስጊዱ “ፈርስት ሂጂራ” ይባላል። በጆርጂያ አቨኑ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ ነው ያለው።

ስፍራው በርካታ አፍሪካ አሜሪካዊያን የሚኖሩበት፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሌሎች ስደተኞችና አሜሪካዊያኑም እየሰፈሩበት የመጣ በከተሜዎቹ አጠራር እያደገ የመጣ “አፕ ኤንድ ካሚንግ” አይነት ነው።

በዚህ ሰፈር ከአምስት አመታት ሀፊት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መስጊድ ሲከፍቱ፤ በራቸው ለሁሉም ክፍት ነበር።

በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የአካባቢው አፍሪካ አሜሪካዊያን ወደዚህ መስጊድ እየመጡ አብረዋቸው ፈጣሪን እንዲያመልኩ፡ ኢትዮጵያዊያኑም እርስ በርስ እንዲተጋገዙና እንዲፈቃቀሩ መንገድ ሆኗል ሲሉ ኢማሙ ነጂብ መሀመድ ይናገራሉ።

“ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆኑ እዚህ አካባቢ ያሉ አፍሪካን አሜሪካንስ፣ አፍሪካኖችም እየመጡ እኛ ጋር ጾም ይፈታሉ።”

ከቅርብና ከሩቅ የተሰባሰቡት እስከ 200 የሚደርሱ ሙስሊሞች በየቀኑ የረመዳን ጾማቸውን የሚፈቱት ማለት የሚያፈጥሩት በፈርስት ሂጂራ መስጊድ ነው።

አፍሪካን አሜሪካዊው መሀመድ ተወልዶ ያደገው መስጊዱ በሚገኝበት ፔትወርዝ ሰፈር ነው። በዚህ አካባቢ ከ10-15 ደቂቃ ተነድቶ የሚኬድባቸው መስጊዶች እንደነበሩ ይገልጻል። አሁን ግን ከቤቱ የመጣው በእግሩ ነው። ቅርበቱ ጥሩነው፤ መስጊዱም የሁላችንም ነው ይላል።

“አላህ ሁላችንም ሙስሊም የሆንን ሁሉ መጥተን በቤቱ ተቀምጠን እንድናመሰግነውና እንድንደሰት ፈቅዶልናል። ይሄ የአላህ ቤት ነው” ብሏል። “የኢትዮጵያዊ ወይንም የአሜሪካዊ ቤት አይደለም። የአላህ ቤት ነው።”

ሰላት ከተሰገደ በኋላ ታዳሚዎች እርስ በርስ እየተጨዋወቱ እራታቸውን በልተው የሚቸኩሉ ወደ ቤታቸው፤ ጊዜ ያላቸውና ለጾሙ ሲሉ ከስራቸው እረፍት የወጡ ደግሞ በመስጊዱ ጸሎታቸውን እያደረጉ ረመዳንን በያመቱ ያከብራሉ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG