በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን “እስራኤል ልታጠቃት ብትነሳ አጸፋው ይጠብቃታል” አለች


ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ
ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ

እስራኤል ኢራን ለማጥቃት አንዲት ስንዝር ብትንቀሳቀስ የታጠቀው የኢራን ሠራዊት የእስራኤልን እምብርት ያጠቃል ሲሉ የእስላሚክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ዛሬ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ “አንቺ ጽዮናዊት አገር አገራችንን ለማጥቃት ስንዝር ታህል ብትንቀሳቀሺ የታጠቀው ሠራዊታችን የጽዮንን እምብርት ኢላማ ያደጋታል” ሲሉ የተናገሩት ዛሬ በተካሄደው የኢራን ወታደራዊ ትዕሪት ላይ ነው፡፡

ንግግራቸው እኤአ በ2015 በቴህራንና በዓለም ኃያላን አገራት መካከል የተካሄደውን ስምምነት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ላይ ያነጣጠረ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

እስራኤል በመካለኛው ምስራቅ የአውቶሚክ የጦር መሳሪያ ያላት ብቸኛዋ አገር ተደርጋ የምትታመን ብትሆንም በኢራን የኒዩክለር ስምምነት የማትገዛና በህደት የኢራን የኒዩክለር ጣቢያዎች ለማጥቃት የተናጥል እምርጃ የምትወስድ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በሶስተኛ ወገን በኩል እኤአ በ2018 በዩናትይድ ስቴትስ የተቋረጠውን የኒውክለር ስምምነት ለማደስ እየተነጋገሩ መሆኑን ተመለክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG