በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ካልፎርኒያ የጣለው ዝናብ የእሳት አደጋ ተከላካዮችን ቢያግዝም የጭቃ ጎርፉ አስግቷል


ቃጠሎ በደረሰበት የመኖሪያ ቤት አካባቢ የጭቃ መንሸራተትን ለመከላከል ሰራተኞች በሥራ ላይ ናቸው፤ በሎስ አንጀለስ ፓሲፊክ ፓሊሳዴስ፣ እአአ ጥር 24፣ 2025።
ቃጠሎ በደረሰበት የመኖሪያ ቤት አካባቢ የጭቃ መንሸራተትን ለመከላከል ሰራተኞች በሥራ ላይ ናቸው፤ በሎስ አንጀለስ ፓሲፊክ ፓሊሳዴስ፣ እአአ ጥር 24፣ 2025።

ዛሬ ሰኞ በደቡብ ካልፎርኒያ የጣለው ተጨማሪ ዝናብ የእሳት አደጋ ሠራተኞችን እያገዘ ቢሆንም እያስከተለ ያለው የጭቃ ጎርፍ፣ በሰደድ እሳት በተቃጠሉ አካባቢዎች የተከማቸውን መርዛማ አመድ እንዲዛመት ያደርጋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

ባለፉት ሳምንታት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በደረሰባቸው የሎስ አንጀለስ፣ አልታዴና እና ካስታይክ ሐይቅ አካባቢ በሚገኘው የፓሲፊክ ፓሊሴድስ አካባቢ የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ መውጣቱን፣ በብሔራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት ውስጥ የሚያገለግሉት የአየር ትንበያ ባለሞያ ጆ ሲራርድ ተናግረዋል። ይህም ከፍተኛ የጭቃ እና የቆሻሻ ፍሳሽ አደጋ እንደሚያስከትልም አመልክተዋል።

የጭቃ ጎርፉ አውራ ጎዳናዎችን ለአደጋ በማጋለጡ፣ በሳንታ ሞኒካ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የትምህርት ቤት ኃላፊዎች በድረ-ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።

በሎስ አንጀለስ የሚገኘው የፓስፊክ ኮስት ዋና አውራ ጎዳናም በጭቃ ጎርፉ ምክንያት ከትላንት እሁድ ከሰዓት ጀምሮ በከፊል መዘጋቱን የካሊፎርኒያ ግዛት የትራንስፖርት ክፍል አስታውቋል።

ሆኖም ከሳምንታት ንፋስ እና ደረቅ የአየር ሁኔታ በኋላ የመጣው ዝናብ፣ በአካባቢው ለሳምንታት ሲቀጣጠል የቆየውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት እንደሚያግዝ ተመልክቷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ያወደመው እና የ11 ሰዎችን ህይወት ያጠፋው የፓሊሴድስ እሳት 90 በመቶ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ የ16 ሰዎችን ህይወት ያጠፋው እና አልታዴና አቅራቢያ የተነሳው እሳት ድገሞ 98 በመቶ በቁጥጥር ስር ውሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG