ናይሮቢ —
በምኅፃር ናሳ (NASA) ተብሎ የሚጠራው የኬንያው ግዙፍ የተቃውሞ ጥምረት ብሄራዊ እምቢ ባይነት ንቅናቄ “የወንጀል ቡድን ነው” ሲል የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴሩ አስታወቀ።
መሥሪያ ቤቱ መግለጫውን ያወጣው የናሳ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ እንደ ፕሬዚደንት ቃለ‑መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ነው።
ኦዲንጋ የዛሬውን ቃለ‑መሃላቸውን በሺሆች በሚቆጠሩ ደጋፊዎች ፊት አደባባይ ላይ የፈፀሙት ያለፈውን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉ አሳውቀው ከምርጫው ከወጡ በኋላ መሆኑ ነው።
ሚኒስቴሩ አድራጎቱን “በመንግሥት ላይ የተፈፀመ ክህደት እና አመፃ” ነው ሲል ከስሷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ