በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ኢኮኖሚ እና በባይደን አስተዳደር ላይ ያሳደረው ጫና


ፎቶ ፋይል፦ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

በአሜሪካውያን ላይ የነዳጅ እና እና የምግብ ዋጋ ማሻቀቡ እና የኢንቬስትመንት ገንዘባቸው እየተነነ መሄዱ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና አስተዳደራቸው ላይ ጫና አሳድሯል።

የዋጋ ግሽበቱ እና የድርሻ ገበያ ዋጋ መውደቁን ተከትሎ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የህዝብ ድጋፍ መጠን ቀንሷል። ይህ የሆነው ወሳኝ የሆኑት የፕሬዚዳንታዊ ሥልጣን አጋማሽ ምርጫዎች ከመንፈቅ ያነሰ ጊዜ በቀራቸው በዚህ ወቅት ነው።

ትናንት የፕሬዚዳንቱን የመራጭ ድጋፍ ማሽቆልቆልን በሚመለከት በጋዜጠኞች የተጠየቁት የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሪን ዣን ፒየር ፕሬዚዳንቱ ለህዝቡ በገቡት ቃል ላይ አትኩረው እየሰሩ ናቸው ብለዋል። በቅርቡ ከፍ ብሎ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ ቁልፍ የድርሻ ዋጋ ሰንጠረዥ (ኤስኤንድፒ 500) በሃያ ከመቶ መውደቁን ተከትሎ ስለተደቀነው አስከፊ የምጣኔ ሃብት ሁኔታ ተጠይቀው ሲመልሱ የአሜሪካ ህዝብ እነዚህን ፈተናዎች በሚገባ ለመጋፈጥ በሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ ፌዴራል ሪዘርቭ የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በዚህ ሳምንት እንደገና የወለድ መጠንን ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG