በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም በአማራ ክልሉ የክተት ዐዋጅ ላይ


አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም
አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አገኘው ተሻገር በተለያዩ ግንባሮ ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት መክፈቱን ገልፀው ይህንን በህልውና ላይ የተከፈተውን ጦርነት ለመመከት ለሚካሄደውና እና የህልውና ዘመቻ በሚል ለጠሩት ዘመቻ እሁድ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም የክተት ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህን ጥሪ ተከትሎም በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞችና በድሬደዋ አደጋውን ለመከላከል ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ ሰዎች ሰልፎች ሲያካሄዱ መስንበታቸው ገልፀን የሰልፉን ተሳታፊዎች ማነጋገራችን ይታወሳል።

በትናንትናው ዕለቱም ቅጥራቸው በሺዎች የሚገም ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰልፍ በባህር ዳር ከተማ መካሄዱን በዘገባችን አስደምጠናል። የባህር ዳር ተቀዳሚ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በሰልፉ ላይ ባሰሙት ንግግር ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውን ህወሓት መደገፉን ማቆም አለበት ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ በአሁኑ ሰዓት ትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ህወሓትን ምላሽ እንዳገኘን እንደምናስደምጣችሁ ገልፀን ለዛሬ በይደር አቆይተነው የነበረ ሲሆን በስልክ ግንኙነት መቋረጥ ምክንያት በቀጥታ ምላሻቸውን ማግኘት ስላልቻልን የክልሉ መንግሥት ተወካይ መሆናቸውን የተናገሩት አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም ምላሽ ሰጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አምባሳደር ፍሰሃ አስገዶም በአማራ ክልሉ የክተት ዐዋጅ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00


XS
SM
MD
LG