በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኅዳሴ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል


የውኃ፣ የመስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ
የውኃ፣ የመስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በመጭው የኢትዮጵያ ዓመት ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የውኃ፣ የመስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ዛሬ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፖሳ አመቻችነት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መሪዎች መካከል ትናንት በኢንተርኔት የቪድዮ ግንኙነት የተካሄደው ስብሰባ የተሳካ እንደነበር አመልክተው በቴክኒክና በሕግ ጉዳዮች ላይ የሚደራደሩት የሃገሮቹ ባለሙያዎች በአንድ ሣምንት ወይም ከዚያ ብዙ ባልራቀ ጊዜ እንደሚገናኙና በቀሪ ነጥቦች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲሠሩ መሪዎቹ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም ኅዳሴ ግድብ ለዚህ ዓመት እንዲይዝ ታቅዶ የነበረውን ውኃ ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ መያዙንና ግድቡን አልፎ መፍሰስ መጀመሩን፣ ውኃውን የመሙላቱ ሥራም ይፋ መሆኑን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኅዳሴ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:36 0:00



XS
SM
MD
LG