በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦነግ ሊቀመንበር ለሰላምና ለ"ነፃና ግልፅ" ምርመራ ጥሪ አሰሙ


ፎቶ ፋይል፦ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ኦቦ ዳዉድ ኢብሳ
ፎቶ ፋይል፦ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ኦቦ ዳዉድ ኢብሳ

በሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈት በእጅጉ ያዘኑ መሆናቸውን በመግለፅ ለቤተሰቡ፣ ለጓደኞቹ፣ ለመላው የኦሮሞና የኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ኦቦ ዳዉድ ኢብሳ የማንም ሲቪል ህይወት በዚህ ዓይነት ሁኔታ ማለፍ እንደሌለበት አሳስበዋል።

ነፃና ግልፅ ምርመራ እንዲካሄድም ለመንግሥት ጥሪ አቅርበዋል።

“በሕዝቦች መካከል ውጥረት እንዲፈጠር ሁልጊዜ የሚጥሩ አሉ” ያሉት ኦቦ ዳውድ የሕዝቡ ህይወት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልተዋል።

ሰዉ የሚሰማውን በነፃነትና በሰላም እንዲገልፅ የፀጥታ ኃይሎችም ህዝቡ ስሜቱን ሲገልፅ “አላስፈላጊ” ያሉትን እርምጃ እንዳይወስዱ አደራ ብለዋል።

ኦቦ ዳዉድ ኢብሳ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦነግ ሊቀመንበር ለሰላምና ለ"ነፃና ግልፅ" ምርመራ ጥሪ አሰሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:02 0:00


XS
SM
MD
LG