በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ንግሥት” ቲና ተርነር አረፈች


ፎቶ ፋይል፦ ዝነኛዋ ድምጻዊት ቲና ተርነር
ፎቶ ፋይል፦ ዝነኛዋ ድምጻዊት ቲና ተርነር

ዝነኛዋ ድምጻዊት ቲና ተርነር በ83 ዓመቷ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች፡፡

ቲና ተርነር ለረጅም ጊዜ በህመም ቆይታ ስዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ማረፏ ተገልጿል፡፡

በችግረኛ የገበሬዎች ማኅበረሰብ ውስጥ አድጋ ከዚያም ባለቤቷ ከነበረው ከአይክ ተርነር ጋር ጥቃት የተመላበት የትዳር ህይወት ያሳለፈችው ቲና ተርነር በኋላ እጅግ ከተዋጣላቸው ዝነኛ ድምጻውያን አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡

የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ተወዳጅነት ባተረፈባቸው በ1950ዎቹ የሙዚቃ ዐለምን የተቀላቀለችው ቲና “የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ንግሥት” ትባል ነበር፡፡ “What's love got to do with it?” በሚለው ዘፈኗ እና በሌሎቹ ስልቶቿ ትታወቃለች፡፡

ቲና ተርነር ስምንት ግራሚ ሽልማቶች ያሸነፈች የተዋጣላት ድምጻዊት ነበረች፡፡

ከሙዚቃ ዓለም ራሷን በጡረታ አግልላ የስዊዘርላንድ ዜግነት የወሰደችው ቲና ተርነር ጀርመናዊውን የሙዚቃ ኩባኒያ ሥራ አስኪያጅ አርዊን ባክን አግብታ ስዊዘርላንድ ትኖር ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG