ዋሺንግተን ዲሲ —
ኳታር ከመጪው የአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት2019ጀምሮ ከኦፔክ አባልነት እንደምትወጣ አስታወቀች። ከነዳጅ አምራች አገሮች ድርጅት ኦፔክ አባልነት እወጣለሁ ያለችው ኳታር፣ የተፈጥሮ ጋዝ አምራች ለመሆን በማቀዷን እንደሆነ ገልፃለች።
የአገሪቱ የኃይል ማመንጫ ጉዳዮች ሚኒስትር ሳአደ ሸሪዳ አልካቢ ናቸው፣ ይህን ያልተጠበቀ ዜና በዛሬው ዕለት ዶሃ ውስጥ ለጋዜጠኞች ይፋ ያደረጉትሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው፣ የዓለማችን ትልቁ የተፈጥሮ ጋዝ አምራቾች፣ ምርቱን በዓመታዊ ምርቱን ከ77 ሚሊዮን ወደ 110 ሚሊዮን ቶን ከፍ ለማድረግ እንዳቀደ አመልክቷል።
ኳታርም፣ የነዳጅ ምርቷን፣ በቀን ከ4.8 ሚሊዮን ወደ 6.5 ሚሊዮን በርሜል ከፍ ለማድረግ ትፈልጋለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ