ፕሬዝደንት ባይደን በመጪው ቅዳሜ የአውስትራሊያ፣ ህንድና ጃፓን መሪዎችን ተቀብለው “ኳድ” በሚል የሚታወቀውን የአራቱን ሃገራት ቡድን ስብሰባ ያስተናግዳሉ። ቡድኑ በተለይም በኢንዶ ፓሲፊክ ቀጠና ባለ ስልታዊ የፀጥታ ትብብር ላይ ያተኩራል። ሕዝብ በብዛት የሚገኝበት ቀጠናው ለቻይናም ከኢኮኖሚ እና ከስልት አንጻር ወሳኝ ነው።
“ኳድ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀውን የህንድ፣ ጃፓን አውስትራሊያ እና አሜሪካ የቡድን ግንኙነት ወደ በለጠ ደረጃ ማሳደግ የፕሬዝደንት ባይደን ዋና ትኩረት እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል።
ኢንዶ ፓሲፊክ በሚል የሚታወቀው ቀጠና አራቱንም ሃገራት የሚነካ እንደሆነ ሲታወቅ፣ ዴለዌር በሚገኘው መኖሪያቸው ስብሰባውን የሚያስተናግዱት ባይደን ልዩ ትኩረት የሚሠጡት እንደሆነም ተነግሯል።
አራቱ ሃገራት በቀጠናው አሳሳቢ በሆኑት ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ እና ሕገ ወጥ የአሳ ማስገርን በተመለከተ የአቋም መግለጫ እንደሚያወጡም ባለሥልታናት ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም