በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኳድ ሚኒስትሮች 'በማስገደድ የሚፈጸሙ’ድርጊቶችን ለመከላከል፣ በአየር ንብረትና በፀረ-ኮቪድ ዘመቻ ለመተባበር ቃል ገቡ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪሴ ፔይን፣ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤስ ጃ ይሻንካር እና የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሺማሳ ሃያሺ ሜልቦርን፤ አውስትራሊያ እአአ ፌብሩዋሪ 11/2022
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪሴ ፔይን፣ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤስ ጃ ይሻንካር እና የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሺማሳ ሃያሺ ሜልቦርን፤ አውስትራሊያ እአአ ፌብሩዋሪ 11/2022

"ኳድ" በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የአራት አገሮች መደበኛ ያልሆነ ቡድን አባላት ዩናይትድ ስቴትስ፣ አውስትራሊያን፣ ጃፓን እና ህንድ፣ “የኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢ ሌሎችን አስገድዶ አንዳች እንዲያደርጉ ከሚያከናወን ማናቸውም ድርጊት የጸዳ መሆኑን ለማረጋገጥ” ባሉት ዕቅድ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ነው ቃል የገቡት።

እያደገ ባለው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እና እያሳየች ነው ባሉት ወታደራዊ መስፋፋት ሳቢያ በቻይና ላይ ከተነጣጠረው እና በተዘዋዋሪ ከተገለጸው ማስጠንቀቂያ ያዘለ መልዕክታቸው በተጨማሪ የአራቱ አገሮች ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ሌሎች ሥጋቶችን በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ የሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የጸረ ሽብር፣ የሳይበር እና የባህር ደኅንነት ጥበቃን እንዲሁም ብርቱ ፈተና የገጠመውን ዓለም አቀፍ የምርቶች አቅርቦት በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ተባብረው ለመሥራትም ቃል ገብተዋል።

ከቡድኑ መሰረታዊ የትኩረት አድማስ ውጪ ቢሆንም፣ ሞስኮን ዓለም አቀፍ ደንቦችን መሰረት ላደረገ ሥርዓት ፈተና ደቃኝ አገር አድርገው የሳሉት የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፤ ኳድ ዓለም አቀፉ ሥርዓት ተጠብቆ እንዲቆይ ያደርጋል የተናገሩትን ጨምሮ በዩክሬን ጉዳይ በምዕራቡ ዓለም እና በሩሲያ መካከል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስም ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳቸው ነበር።

XS
SM
MD
LG