በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የአራቱን አገራት መሪዎች በአካል ሰበሰቡ


 የዩናትድ ስቴትስ ፣የጃፓን፣ የአውስትራሊያና የህንድ መሪዎች
የዩናትድ ስቴትስ ፣የጃፓን፣ የአውስትራሊያና የህንድ መሪዎች

የዩናትድ ስቴትስ የጃፓን፣ የአውስትራሊያና የህንድ መሪዎች፣ በትናንትናው እለት በዋይት ሀውስ በአካል ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ኳድ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የአራቱ አገሮች ስብስብ ኢንዶ ፓስፊክ በሚባለው የዓለም ክፍል ዴሞክራሲን ለመጠበቅ ቁርጠኝነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአራቱም አገራት የጋራ መነጋገሪያ ስለሆነችው ቻይና ግን በግልጽ ያስታወቁት ነገር የለም፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው በአካል ተገናኝተው ስብሰባ ሲያካሂዱ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

ባይደን የተሰበሰቡት ከአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስካት ሞሪሰን፣ ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲና ከ ከጀፓና ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋ ጋር ነበር፡፡

ጆ ባይደን አብረው ሆነው ባሰሙትም ንግግር “እኛ አራት ዋነኞቹ የዴሞክራሲ አገሮች የረጅም ጊዜ የትብብር ታሪክ አለን፡፡ ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ እናውቃለን የገጠመነንም ፈተና እንወጣለን” ብለዋል፡፡

“ቀጠናውን ክፍት ዲሞክራሲያዊና የተረጋጋ ለማድረግ ያለመ” መሆኑን የገለጹት የአገራቱ መሪዎች፣ ቻይናን በይፋ ባይጠቅሱም በዝግ በሚያደርጉት ስብሰባቸው ዋነኛ ጉዳያቸው ቤጂንግ እንደምትሆን ተገምቷል፡፡

ትናንት ዓርብ ስብሰባውን የተቹት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሆ ሌጂንግ ሌሎች አገሮችን ኢላማ በማድረግ የተቧደነው ዝግ ስብሰባ በአካባቢው አገሮች መካከል ያለውን የዘመኑን ትብብርና መነሳሳት ይቃረናል፡፡ ምንም ድጋፍ የማያገኝ ሲሆን ውድቀትን ያስከትላል” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG