በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንቀጽ 39 እና የቅማንት ኢትዮጵያውያን ጥያቄ


የኢትዮጲያ ካርታ
የኢትዮጲያ ካርታ

የቅማንት ሕዝብ የኢትዮጵያው ህገ-መንግሥት አንቀጽ 39 የሰጠን መብት ይከበርልን በማለታችን ስቃይ እየደረሰብን ነዉ ይላሉ።

የቅማንት ሕዝብ፣ የኢትዮጵያው ህገ-መንግሥት አንቀጽ 39 የሰጠዉ መብት ይከበርልን በማለቱ እስራት፣ ግድያ፣ መሰደድና ወከባ እየደረሰበት በማለት በርካታ የቅማንት ተወላጆች ነን ያሉ አድማጮቻችን ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪና የኢሜይል መልዕክት አድርሰውናል። የፈዴራሉ መንግሥት መብቱ እንዲጠበቅ ፈቅዶ ሳለ፣ እምቢተኛነቱና እየደረሰብን ያለው ስቃይ ከክልሉ መንግሥት የሚሰነዘር ነው ሲሉም ይናገራሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪ የሆኑ ሦስት የቅማንት ተወላጆችን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግሯል። እንግዶቹ ወ/አበባ ተፈሪ ከሲያትል፣ ዋንግተን፤ አቶ አበበ ንጋቱ ከዳላስ፣ ቴክሳስ፤ እንዲሁም እና አቶ ፋሲል ካሰኝ ከአትላንታ ጆርጂያ ናቸው።አዲሱ አበበ ያዘጋጀውን ዘገባ ለማዳመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

አንቀጽ 39 እና የቅማንት ኢትዮጵያውያን ጥያቄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:20 0:00

XS
SM
MD
LG