በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉዞ ወደ ካታር - የዓለም ዋንጫ

A computer generated image of Lusail Stadium that will host the 2022 FIFA World Cup final, with seating capacity of 80,000, in Lusail City, north of central Doha, Qatar. Qatar Supreme Committee for Delivery and Legacy/Handout via

ኢትዮጵያና ሌሶቶ ባዶ ለባዶ፣ ቡሩንዲና ኤርትራ ሁለት ለአንድ ተለያይተዋል።

ካታር እአአ በ2022 ዓ.ም. ለምታዘጋጀው መጭው የዓለም ዋንጫ ቅድመ-ማጣርያ የመጀመሪያ ጨዋታ የሌሶቶን ብሔራዊ ቡድን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባዶ ለባዶ ተለያይቷል።

በባህር ዳር ስታድየም ላይ በተደረገው ጨዋታ ሙጂብ ቃሲም እና አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኙዋቸውን የጎል ዕድሎች ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል።

የዋልያዎቹ አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ ጨዋታውን ማሸነፍ ባይችሉም ተጫዋቾቻቸውን አድንቀዋል።

የሌሶቶ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በመጭው ዕሁድ ይደረጋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን አሥመራ ላይ ባደረገው ግጥሚያ በናሚቢያ አቻው ሁለት ለአንድ ተሸንፏል።

“ሬድ ሲ ካመልስ” እየተባለ የሚጠራው የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካና አውስትራሊያ ቡድኖች ውስጥ የሚጫወቱ አሥራ አራት ተሰላፊዎች ቢኖሩትም ዘጠኙ አሥመራ የገቡት ትላንት ለግጥሚያው የገቡት ሦስቱ ብቻ መሆናቸው ታውቋል።

በሌላ የስፖርት ዜና - የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ማኅበር አሠልጣኝ መቅጠሩን አስታውቋል።

ለተጨማሪና ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጉዞ ወደ ካታር - የዓለም ዋንጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG