አዲስ አበባ —
ቀደም ሲል በኦሮምያ በሶማሌ ድንበር በአለፉት ሳምንታት ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች የተከሰተው ብጥብጥና ሁከት እንደሚያሳስባቸው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ገለፁ፡፡
በዚሁ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነም አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክል ሬነር በአዲስ አበባ ባደረጉት የመጀመሪያ ቃለ ምልልስ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ ሽብር ሕጉን እየተጠቀመ ያለበት ሁኔታ ዩናይትድ ስቴትስን እንደሚያሳስባት ይበልጡኑ ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በመግለፃቸው ምክንያት የታሰሩ ሰዎች ጉዳይም በደንብ መታየት እንዳለበት አምባሳደሩ አስታውቀዋል፡፡
ነገ በሀገራቸው በሚከበረው የምስጋና ቀን /ታንክስ ጊቪግ/ ዋዜማ አምባሳደር ማይክል ሬነርን በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ነው ተከታዩን ልኳል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ