በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂንፒንግ እና ፑቲን በቤጂንግ የክረምት ኦሊምፒክ ዋዜማ ተነጋገሩ


የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የቻይናው መሪ ቺ ጂንፒንግ 
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የቻይናው መሪ ቺ ጂንፒንግ 

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን እና የቻይናው መሪ ቺ ጂንፒንግ ጋር ዛሬ ዓርብ ከቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ መክፈቻ ሥነ ስርዓት በፊት ተገናኝተው መነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡

ሁለቱ አገሮች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር እየሻከረ ከመጣው ግንኙነታቸው አንፃር ያላቸውን አንድነት የሚገልጹበት መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የሩሲያው መንግሥት ዜና አገልግሎት ታስ ፑቲን “በመከባበር ላይ የተመሰረተ የሁለቱ አገሮች እድገት የሚጠቀም ግንኙነት መሆኑን” መናገራቸውን ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሩሲያው ሩቅ ምስራቅ ግዛት እስከ ቻይና ድረስ የሚዘልቅ የ10 ቢሊዮን ኪዩቢክ ነዳጅ በየዓመቱ ለቻይና ለማቅረብ ማቀዷንም አስታውቀዋል፡፡

እንደ ሩሲያ ባለሥልጣኖች ከሆነ የሁለት አገር መሪዎች በዚህ ጉብኝት ከ15 በላይ የሚደርሱ ሥምምነቶችን እንደሚፈራረሙ ተነግሯል፡፡

እኤአ በ2021 ሁለቱ አገሮች ከእስከዛሬው ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበበትን የ146 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡ ፑቲን ይህን ግንኙነት ወደ 200 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረግ እንደሚቻል ለቻይናው ፕሬዚዳንት ቺ ጂንፒንግ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ ከየትኛውም የዓለም መሪ ጋር በአካል ያልተገናኙት የቻይናው መሪ ቺ ጂንፒንግ የሁለቱ አገሮ ግንኙነቶች ወዳጅነታቸውን የበለጠ እንደሚያጠናክርና ፍሬያማ እንደሚሆን መግለጻቸውን የቻይና መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳ ሁለቱ አገሮች መልክ የያዘ አንድነት ባይኖራቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዩናይትድ ስቴትስን ተፅዕኖ በጋራ ለመቋቋም ትብብራቸውን እያጠነከሩ መምጣታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG