በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን በሳይቤሪያ የገበያ አዳራሽ የእሳት ቃጠሎ ተጠያቂ ያሏቸውን "ቅጣት ያገኛሉ" አሉ

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን
የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

ባለፈው እሑድ በአንድ የሳይቤሪያ የገበያ አዳራሽ የተነሳው፣ ብዙዎቹ ህፃናት ለሆኑበት ለ64 ሰዎች ሞት ምክንያት ለሆነው የእሳት ቃጠሎ ተጠያቂ ለሆኑት፣ ተገቢውን ቅጣት እንደሚሰጧቸው፣ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አስታወቁ።

ባለፈው እሑድ በአንድ የሳይቤሪያ የገበያ አዳራሽ የተነሳው፣ ብዙዎቹ ህፃናት ለሆኑበት ለ64 ሰዎች ሞት ምክንያት ለሆነው የእሳት ቃጠሎ ተጠያቂ ለሆኑት፣ ተገቢውን ቅጣት እንደሚሰጧቸው፣ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አስታወቁ።

በድጋሚ የተመረጡት ፕሬዚዳንት ይህን ቃል የተናገሩት ዛሬ ማክሰኞ፣ ቃጠሎው ወደተነሳባት የኢንዲስትሪ ከተማዋ ኬሜሮቮ ከበረሩ በኋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ እዚያ እንደደረሱ፣ ለሰላባዎቹ መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው፤ ነገ ረቡዕ ደግሞ ብሔራዊ የኃዘን ቀን እንደሚሆን ይፋ አድርገዋል።

በነገሩ የተቆጡ ብዙ ሺህ ተሰላፊዎች በከተማዋ ዋና ዓደባባይ በመውጣት፣ ቃጠሎው በነፃ ምርመራ እንዲጣራላቸው ጠይቀው፣ ነገሩን ለማድበስበስ የሚሞክሩ አንዳንድ ባለሥልጣናትን ደግሞ መክሰሳቸው ታውቋል።

ቃጠሎው የተነሳው ትምህርት ቤቶች በተዘጉበትና በገበያ አዳራሹም በርካታ ህፃናት በሚገኙበት ወቅት በመሆኑ፣ በሕዝብ ዘንድ ይበልጥ ቁጣና ንዴት እንደቀሰቀሰ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG