ዋሺንግተን ዲሲ —
የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሀገቸው ወታደሮች በርከት ካሉ የሶሪያ ግዛቶች እንዲወጡ ማዘዛቸውን ዛሬ አስታወቁ።
ፕሬዚደንቱ ይህን ያስታወቁት ሶሪያዋ ላታኪያ ክፍለ ሀገር ባለው የሩስያን ሂሚዪም የአየር ኃይል ሰፈር በተገኙበት አስቀድሞ ይፋ ያልተደረገ ጉብኝት ሲሆን፣ የሶሪያ ፕሬዚደንት ባሻር አል አሳድ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
የሩስያ ኃይሎች የፕሬዚደንት አሳድን የጦር ሰራዊት ሊረዱ ውጊያውን የተቀላቀሉት ከሁለት ዓመት በፊት እንደነበር ይታወሳል።
የሩስያው ፕሬዚደንት በዛሬው ንግግራቸው የሀገራቸውን የሶሪያ ኃይሎች አብዛኞቹን ለውጊያ ዝግጁ የሆኑ ዓለም አቀፍ ሽብርተኞች ድል መተዋል ብለዋል።
“የእስልማዊ መንግሥት” ብሎ ራሱን የሚጠራውን ቡድን ማለታቸው ነው።
የሶሪያው ፕሬዚደንት ሩስያ በሶሪያ ፀረ ሽብርተኛ ጦርነት ውስጥ ስለተጫወተችው ሚና አመስግነዋቸዋል ሲሉ የሶሪያ የመንግሥት ዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል።
ፕሬዚደንት ፑቲን ሶሪያን ሲጎበኙ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ