በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን ተቃውሞ የገጠመው ሕግ አፅድቀዋል


የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾና ተቃዋሚ ፖለቲከኞ የዴሞክራሲን ሂደት ያስተጓጉላሉ በሚል የኮነኑትን ረቂቅ ሕግ አጽድቀዋል፡፡

ዛሬ ታኅሣሥ 21 ሥራ ላይ መዋሉ የተነገረው ይህ ሕግ፣ በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት የውጭ ተቋማትን ጥቅም ሊያስጠብቁ ይችላሉ የሚባሉትን የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ሕግ ግለሰቦችና ሕዝባዊ ተቋማትን እንደ “ውጭ አካላት ወኪል” አድርጎ ሊያስፈርጃቸው በሚችለውና ቀድሞውኑንም አነጋጋሪ በነበረው ሕግ ላይ ተጨማሪ ሆኖ የወጣ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ሊፈረጁ ይችላሉ የተባሉ ተቋማትም እንቅስቃሴዎቻቸውን የገንዘብ ምንጮቻቸውን እንዲያስመረምሩ ያስገድዳቸዋል።

ፑቲን በፊርማቸው ባጸደቁት ሌላኛው ተጓዳኝ ሕግ መሰረት የውጭ ወኪሎች ሆነው የተፈረጁ ተቋማት ገንዘባቸውናን እንቅስቃሴዎቻቸውን የማያስመዘግቡ ከሆነ እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ በሚችል እስራት ይቀጣሉ፡፡

እንደ ውጭ አካላት ወኪል አድርጎ ከሚያስፈርጁ ነገሮች ውስጥ የውጭ አካላትን ጥቅም ለማስጠበቅ፣ የፖለቲካ ተቃውሞ ሰልፎችን፣ የፖለቲካ ክርክሮችን ማካሄድ፣ ወይም በመንግሥት ፖሊሲዎች ላይ አስተያየት መስጠት፣ በምርጫ ውጤቶች ወይም ሕዝብ ውሳኔዎች ላይ ተመስርቶ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን መስጠትን ያጠላል፡፡

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል በራሽያ የወጣን ሕግ የተቃወመ ሲሆን “ህጉ በሩሲያ ውስጥ ሆነው እርዳታዎችን ከውጭ ለጋሽ ድርጅቶች የሚቀበሉትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች በርካታ ድርጅቶችንም የሚጎዳ እርምጃ ነው በማለት አውግዞታል፡፡

ይህ ህግ በሩሲያ የሚገኙትን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የሚጎዳና ሲጎዳ የቆየም ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሠሩትን ተሟጎች ሁሉ የሚጎዳ ነው ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG