በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን በዩክሬን የሚገኙ ምዕራባውያን ወታደሮች ወደ ሦስተኛ የዓለም ጦርነት ሊመሩ ይችላሉ አሉ


የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ እአአ መጋቢት 18/2024
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ እአአ መጋቢት 18/2024

ምዕራባውያን ወታደሮች በዩክሬን መስፈራቸው፣ ዓለምን ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ሊገፋ የሚችል ነው ሲሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስጠነቀቁ። ፑቲን ይህን ያሉት ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ሰኞ ጠዋት በሞስኮ ባደረጉት ንግግር ነው። ፑቲን አክለው "ማንም ግን እንደዛ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የመግባት ፍላጎት አለው ብዬ አላስብም"ብለዋል።

ፑትን በንግግራቸው የሩሲያ ታጣቂ ኃይሎች በየቀኑ ዩክሬን ውስጥ እየገፉ መሆኑን እና ሞስኮ በጦርሜዳ ድል እያገኘች መሆኑን ገልጸዋል።

ፑቲን ስለፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ ፈረንሳይ ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት መንገዶችን ትፈልጋለች የሚል እምነት እንደነበራቸው እና አሁንም ተስፋቸው እንዳልተሟጠጠ ተናግረዋል።

ማክሮን በፓሪስ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ወቅት በዩክሬን ተኩስ ማቆም እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫም ለዩክሬን የሚያቀርቡትን የጦር መሳሪያ እንዲያቆሙ እንደጠየቋቸው 'ታስ' የተሰኘው የሩሲያ የዜና ተቋም ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG