በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ፑቲን ፒተርስበርግ የደረሰው ፍንዳታ የሽብርተኝነት ተግባር ነው አሉ

የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን
የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን

ትናንት ረቡዕ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ የደረሰው ፍንዳታ የሽብርተኝነት ተግባር ነው ሲሉ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ተናገሩ።

ትናንት ረቡዕ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ የደረሰው ፍንዳታ የሽብርተኝነት ተግባር ነው ሲሉ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ተናገሩ።

ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት ሶሪያ ውስጥ ላገለገሉ ሩስያውያን ወታደሮች ዛሬ ክሬምሊን ቤተ መንግሥት ውስጥ ባደረጉት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። ፑቲን ስለፍንዳታው በዝርዝር አልገለፁም።

ቤት ውስጥ በተሰራ ፈንጂ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ አሥራ ሦስት ሰዎች ቆስለዋል።

መርማሪዎች መጀመሪያ ላይ ጥቃቱን የግድያ ሙከራ ሲሉ ገልጸውት ነበር፣ ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወገን እስካሁን የለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG