በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን "በኒውክሊየር መሣሪያ ቅነሳ ውሉ መሳተፍ እናቆማለን" አሉ

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባለን የኒውክሊየር መሣሪያ ቁጥጥር ውል መሳተፋችንን እናቆማለን ሲሉ ተናገሩ።
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባለን የኒውክሊየር መሣሪያ ቁጥጥር ውል መሳተፋችንን እናቆማለን ሲሉ ተናገሩ።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባለን የኒውክሊየር መሣሪያ ቁጥጥር ውል መሳተፋችንን እናቆማለን ሲሉ ተናገሩ።

በእንግሊዝኛ የአህፅሮት ስሙ "ኒው ስታርት" ተብሎ የሚጠራው እና በሁለቱ ሀገሮች መካከል እአአ 2010 የተደረሰው የመጨረሻው ውል ሁለቱም ሀገሮች ከ1550 በላይ የኒውክሊየር ቦምቦች እንዳያከማቹ የሚቆጣጠር ሲሆን ውሉ ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜ እአአ በ2026 ያበቃል።

ፑቲን ለሩሲያ ፓርላማ ዛሬ ባደረጉት የሀገር ሁናቴ መግለጫ ንግግር "አሁኑኑ ከውሉ ሙሉ በሙሉ እንወጣለን ማለት አይደለም" ብለዋል።

አስከትለውም "ዩናይትድ ስቴትስ የኒውክሊየር መሣሪያ ሙከራ ካደረገች እኛም ሙከራችንን ለመቀጠል ዝግጁ መሆን አለብን" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG