በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሩሲያ የኑክሌር ኃይሏን ለመጠቀም ዝግጁ ናት” ፑቲን


የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የአገራቸው ሉዓላዊነት እና ነፃነት አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ፣ ሩሲያ የኑክሌር ኃይሏን ለመጠቀም ዝግጁ መኾኗን ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን አስጠነቀቁ።

በመጪው ዓርብ በሚደረገው የሩሲያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ጥርጥር እንደሌለውና ለተጨማሪ የስድስት ዓመታት የሥልጣን ዘመን እንደሚቆዩ የሚነገርላቸው ፑቲን፣ ምዕራቡን ዓለም በግልፅ ሲያስጠነቅቁ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።

ፑቲን ማስጠንቀቂያውን የሰጡት፣ በሩሲያ ቴሌቪዥን ዛሬ ረቡዕ በተለቀቀ ቃለ ምልልስ ላይ፣ በዩክሬን በሚካሄደው ጦርነት የኑክሌር መሳሪያ ለመጠቀም ዝግጁ ሆነው እንደሁ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው።

እስከ አሁን የኑክሌር መሣሪያ መጠቀምን አስፈላጊ ሆኖ እንዳላገኙት የተናገሩት ፑቲን፣ የአገራቸው ሉዓላዊነት እና ነፃነት አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ ግን ሩሲያ የኑክሌር ኃይሏን ለመጠቀም ዝግጁ ናት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG