የሩሲያ ፓርላማ አገሪቱ በመጪው መጋቢት ምርጫ እንደምታካሂድ ቀን ሲቆርጥ፣ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ ግዜ እንደሚወዳደሩ በሰፊው እየተጠበቀ ነው።
ምርጫው በፈረንጆቹ አቆጣጠር መጋቢት 17 እንዲካሄድ ም/ቤቱ ዛሬ ሐሙስ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።
ፕሬዝደንት ፑቲን እስከ አሁን በምርጫው እንደሚወዳደሩ ባያስታውቁም፣ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ግን በሰፊው በመጠበቅ ላይ ነው።
በእርሳቸው መሪነት በተደረገው የሕገ መንግስት ማሻሻያ መሠረት፣ ለሁለት የስድስት ዓመት የሥልታን ዘመን መመረጥ እንደሚችሉ ታውቋል። ይህም የ71 ዓመቱን ፑቲን፣ እ.አ.አ እስከ 2036፣ ለተጨማሪ 12 ዓመታት መሆኑ ነው፣ ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።
ሊገዳደሯቸው የሚችሉት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ እስር ቤት ተጥለዋል፣ አለዚያም አገር ጥለው ወጥተዋል። ገለልተኛ የመገናኛ ብዙሃንም እንዳይሰሩ ታግደዋል።
መድረክ / ፎረም