የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ለተጨማሪ የስድስት ዓመት የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ዛሬ አረጋገጡ፡፡
ፑቲን በምርጫው እንደሚወዳደሩ ያስታወቁት የሩስያ ፓርላማ ላዕላይ ምክር ቤት ቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እ አ አ መጋቢት 17 2024 ዓመተ ምሕረት እንዲካሄድ መወሰኑን ማግሥት ነው፡፡
ፑቲን እንደገና ለመመረጥ እንደሚወዳደሩ በክሬምሊን ቤተ መንግሥት የተዘጋጀ ሥነ ስርዓት ተከትሎ በሩስያ መንግሥት ቴሌቭዥን አስታውቀዋል፡፡
ፑቲን ሌተና ኮሎኔል አርቲዮም ዦንጋ ከተባሉ ወታደራዊ መኮንን ጋር ሲወያዩ “ በየጊዜው ሓሳቤን ስቀያይር ነበር ፡፡ አሁን ግን ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡ እወዳደራለሁ” ማለታቸውን የመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ማለታቸውን የጦር መኮንኑን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የካርኒጊ የሩስያ አና ዩሬዥያ ማዕከል ተንታኟ ታታኒያ ስታኖቫያ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል ፑቲን በምርጫው እንደሚወዳደሩ መደበኛ መግለጫ ሳይሆን ባልተጋነነ መንገድ እንዲያስታውቁ የተደረገው ሥራቸውን መስራታቸውን እንጂ ለሆሆታ ደንታ የሌላቸው ተደረገው እንዲታዩ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል፡፡
ተንታኞች እንደሚሉት በሩስያ ከማናቸውም ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩት ቪላዲሚር ፑቲን እቀናቀናለሁ የሚል ቢነሳ ዕጣው መታሰር ወይም ደብዛው መጥፋት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ በድጋሚ ይመረጣሉ፡፡
በፑቲን ዘመነ መንግሥት የሩስያ ምርጫ ፍትሃዊም ሆነ እና ግልጽ ሆኖ አያውቅም፡፡
መድረክ / ፎረም