በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትራምፕ የኔቶ አቋም በአሜሪካ ውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ መከፋፈልን ፈጥሯል


የትራምፕ የኔቶ አቋም በአሜሪካ ውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ መከፋፈልን ፈጥሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:23 0:00

የትራምፕ የኔቶ አቋም በአሜሪካ ውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ መከፋፈልን ፈጥሯል

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ፣ ከሀገር ውስጥ ብዙኀን መገናኛ ጋራ በነበራቸው ቃለመጠይቅ፣ “ሩሲያ ከዶናልድ ትራምፕ ይልቅ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለሁለተኛ ዙር ቢመረጡ ትሻለች፤” ያሉ ሲኾን፣ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ፣ የሰሜን አትላንቲክ የቃል ኪዳን ጦር ኔቶ ላይ ያላቸውን አቋም ቁርጠኝነት በድጋሚ አንጸባርቀዋል። ባይደን በበኩላቸው፣ ትራምፕ የሀገራትን የኔቶ አባልነት አቋም አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት፣ “አደገኛ፣ አሜሪካዊ ያልኾነና አስደንጋጭ” ሲሉ ተችተውታል።

የሁለቱ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች፣ ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የሚኖራትን ሚና አስመልክቶ ያላቸው የአቋም ልዩነት እና ክፍተት ጎልቶ ወጥቷል።

በአሶሺየትድ ፕሬስ እና በአሜሪካ ድምፅ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳስኩዋራ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG