በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መንግሥታት ጥሪ አቀረቡ


ቭላድሚር ፑቲን እና ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን
ቭላድሚር ፑቲን እና ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን

ተቀናቃኝ መንግሥታት በሚዋጉባት በሊቢያ ከፊታችን ዕሁድ ጀምሮ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሩስያ እና የቱርክ መንግሥታት ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ቭላድሚር ፑቲን እና ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትናንት ኢስታንቡል ላይ ባወጡት የጋራ መግለጫ ሊቢያ ውስጥ ያለውን ግጭት በወታደራዊ መንገድ ለመፍታት መሞከሩ የህዝቡን ስቃይ እና ክፍፍሉንም ከማባባስ በቀር ውጤት አይኖረውም ብለዋል።

ህገወጥ ፍልሰት የጦር መሳሪያ በህገ ወጥ መንገድ ማስተላለፍ እና ሽብርተኝነት የሊቢያው ጦርነት ካስከተላቸው መዘዞች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል መሪዎቹ።

ቱርክ ትሪፖሊ ላይ ተቀማጩን በምዕራባውያን የሚደገፈውን መንግሥት ለመርዳት ወታደሮች መላክ ጀምራለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ ሳራጅ ትናንት ረቡዕ ከአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ብረሰልስ ውስጥ ተገናኝተው ተወይይተዋል። የእርሳቸው ተቀናቃኝ ጀነራል ኻሊፋ ሃፍታር በበኩላቸው ከደጋፊያቸው የኢጣሊያ ጠ/ሚ ጁሴፔ ኮንቲ ጋር ተወይይተዋል።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄይኮ ማስ ሁሉም ወገኖች ሊቢያን ሁለተኛ ሶሪያ ከመሆን እንዲታደጉ አሳስበው፣ የጦር መሳሪያ ማዕቀብም ይጣል፤ ፖለቲካዊ መፍትሄም ይፈለግ ሲሉ ተማጽነዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG