በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፑንትላንድ ኃይሎች ቦሳሶ አቅራቢያ ከእስልማዊ ሸማቂዎች ጋር እየተፋለሙ ናቸው


ፕሬዝደንት አብዲራህማን ፋሮሌ
ፕሬዝደንት አብዲራህማን ፋሮሌ

ባሪ በሚባለው በምዕራቡ የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ቦሳሶ ከተማ አቅራቢያ በፑንትላንድ ኃይሎችና በስላማዊ ተዋጊዎቹ መካከል ከባድ ውጊያ ተካሂዷል።

የፑንትላንድ ፕሬዚደንት አብዲራህማን ፋሮሌ ዛሬ ማለዳው ላይ ባካባቢው በነበሩ የመንግሥቱ የጸጥታ ጥበቃ ኃይሎች ላይ ተኩስ በመክፈት ውጊያውን የቀሰቀሱት ሽምቅ ተዋጊዎቹ እንደሆኑ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የተወሰኑት ሽምቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል የጥቃቱን መሪም ይዘናል ሲሉም አክለዋል

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስላማዊ ነውጠኞችን ፑንትላንድ እንድታጠፋ ይርዳጋ ሲሉም ፕሬዚደንቱ ተማጽኖ አቅርበዋል። ካላጠፋናቸው በጠቅላላ ባካቢቢው መስፋፋታችው ነው ሲሉም እስጠንቅቀዋል።

የፑንትላንድ መንግሥት ሰሞኑን በሞሐመድ ሳይድ ኦቶም የሚመራውን የአልኢትሃድ አልኢስላሚያ ነውጠኛ ቡድን ርዝራዦሮች ለማጥፋት ዘመቻ ሊጀምር ሲዘጋጅ ቆይቷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትም ማዕከላዊ እና ደቡባዊ ሶማሊያን በአብዛኛው ለሚቆጣጠረው ለአልሸባብ ተዋጊ በዋናነት ከሚያቀርቡለት አንዱ አቶም እንደሆነ ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG