በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑንትላንድ ‘አንድ ሰው - አንድ ድምፅ’ የሚለውን በመተው፣ ጎሳን መሠረት ያደረገ ምርጫ ልታካሂድ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የፑንትላንዱ ፕሬዝደንት ሳይድ አብዱላሂ ደኒ
ፎቶ ፋይል፦ የፑንትላንዱ ፕሬዝደንት ሳይድ አብዱላሂ ደኒ

በሶማሊያ የምትገኘው ራስ ገዟ ፑንትላንድ፣ በሚቀጥለው ዓመት በምታካሂደው ምርጫ ‘አንድ ሰው - አንድ ድምፅ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ አሠራር ለመከተል አቅዳ የነበረ ቢሆንም፣ እቅዱን በመተው ውስብስብ ነው የሚባለውንና በጎሳ ላይ የተመሠረተውን ምርጫ ለማካሄድ እንደወሰነች የኤኤፍፕ ዘገባ አመልክቷል።

ባለፈው ግንቦት ባካሄደችው የአካባቢ ም/ቤት ምርጫ፣ ‘አንድ ሰው - አንድ ድምፅ’ የሚለውን የምርጫ መርህ ከአምሳ ዓመታት በኋላ ተግባራዊ በማድረጓ፣ ዓለም አቀፍ አድናቆት ተችሯት ነበር። ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን፣ የፑንትላንዱ ፕሬዝደንት ሳይድ አብዱላሂ ደኒ፣ የምርጫ ሂደቱን ለራሳቸው መጠቀሚያ አድርገዋል፣ እንዲሁም በመጪው ጥር የሚያበቃውን የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሕገ መንግስቱን ለማራዘም ሞክረዋል የሚል ውንጀላ አሰምተዋል።

ፕሬዝደንት ደኒ ትናንት ማምሻውን እንዳስታወቁት፣ የፓርላማ ምርጫው በመጪው ታህሳስ 29 የሚካሄድ ሲሆን፣ የጎሳ ተወካዮች 66 የፓርላማ ዓባላትን ይመርጣሉ።

“ወደዚህ አማራጭ በመግባቴ አዝናለሁ” ብለዋል ፕሬዝደንቱ ምክንያቱን ሳያብራሩ።

ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ውሳኔውን በመልካም ተቀብለዋል። ውሳኔው በፓርላማው መጽደቅ ይኖርበታል።

የፑንትላንድ ጎረቤት በሆነችውና በእ.አ.አ 1991 የራሷን ነጻነት ባወጀችው ሶማሊላንድ ቀጥተና ምርጫ የተካሄደ ቢሆንም፣ ዓለም አቀፍ እውቅና ግን ሳይቸራት ቀርቷል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ፣ ጎሳን መሠረት ያደረገው እና ውስብስብ ነው የሚባለውን የምርጫ ሂደት በመጪው የፈረንጆች ዓመት ለመተው አቅደዋል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG