በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሔሪኬን ማሪያ ለተጎዳችው ፖርቶ ሪሎ የዕዳ ስረዛ

በከባድ ንፋስ በነጎደው ከብድ ዝናብ ሔሪኬን ማሪያ ለተጎዳችው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ፖርቶ ሪኮ እንድታገገም ዕዳዋ እንዲሰረዝላት ሲሉ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ቢናገሩም የዋይት ሃውስ የበጀት ዳይሬክተር ሚክ ማልቩኒ ግን ፌዴራሉ መንግሥት የደሴቲቱን ዕዳ እንደማይከፍላልት ዛሬ አስታውቀዋል።

በከባድ ንፋስ በነጎደው ከብድ ዝናብ ሔሪኬን ማሪያ ለተጎዳችው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ፖርቶ ሪኮ እንድታገገም ዕዳዋ እንዲሰረዝላት ሲሉ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ቢናገሩም የዋይት ሃውስ የበጀት ዳይሬክተር ሚክ ማልቩኒ ግን ፌዴራሉ መንግሥት የደሴቲቱን ዕዳ እንደማይከፍላልት ዛሬ አስታውቀዋል።

አስተዳደሩ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት፣ የገንዘብና ሌላም ዕርዳታ እንዲደረግላት ሃሳብ ያቀርባል እንጂ ዕዳቿን አንከፍልም ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ትናንት ፖርቶ ሪኮ ዋና ከተማ ሳን ሁዋን ጉብኝታቸው ላይ ለፋክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የፌዴራሉ መንግሥት ባለልሥጣናት የደሴቲቱን የዕዳ ሁኔታ እንደገና እንደሚገመግሙ ገልፀው መሰረዝ ይኖርብናል ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ በዚህ አባባላቸው መንግሥት የዕዳ ማቅለያ ሊረዳት ይሁን ወይም መዋዕለ ነዋይ መዳቢዎችን ለኪሳራ በሚዳርግ መልኩ የዕዳ ማስተካከያ ሊያደርግላት እንደሆን ግልፅ አላደረጉም።

በተደጋጋሚ ግን ደሴቲቱ እንዳታገግም የዕዳው ጉዳይ ትልቅ እንቅፋት መፍጠሩን ገልፀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ዋይት ሃውስ ለፖርቶ ሪኮና ለሌሎችም በተፈጥሮ አደጋዎች ለተመቱ አካባቢዎች ኮንግሬስ የሃያ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ጥቅል እንዲፈቅድ ለመጠየቅ እይተዘጋጀ መሆኑን ስማቸው ያልተገለፀ የቤተ መንግሥቱ ምንጮች ጠቁመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG