ዋሺንግተን ዲሲ —
በሰሜን አፍሪካይቱ ሀገር ቱኒዚያ መንግሥት የወሰደውን የቁጠባ እርምጃን በመቃውም ለሦስት ቀናት ያህል በተካሄደው ግጭት የታከለበት ሰልፍ ከ5መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች መታሰራቸውን ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።
መንግሥት ባወጣው አዲስ ባጀት ላይ የግብር ክፍያ በመጨመሩ ምክንያት ባለፈው ሰኞ የጀመረውን ተቃውሞ ለማርገብ የፀጥታ ኃይሎች በብዙ ከተማዎች ተመድበዋል። ትላንት ብቻ ከ3መቶ ሰዎች በላይ መታሰራቸውን ባለሥልጣኖች ጠቁመዋል።
ተቃዋሚዎቹ ጀርባ በተባለው የቱሪስቶች መስህብ በሆነው ደሴት ላይ በሚገኝ የአይሁዳውያን ትምህርት ቤት ላይ ቤት ውስጥ የተሰራ የቤንዚን ቦብም ወርውረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ