በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱኒዥያ ውስጥ ተቃዋሚዎች የፖሊስ ጣቢያ አቃጠሉ


በደቡባዊ ቱንዥያ አግረብ ከተማ ተዘግቶ የቆየው ከተማ ቆሻሻ መድፊያ ስፍራ እንዲከፈት ባለሥልጣናቱ መወሰናቸው ያስቆጣቸው ተቃዋሚዎች በከተማዋ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማቃጠላቸውን እማኞች ገለጹ።

ተቃውሞው የተቀጣጠለው ትናንት ፖሊሶች በተኮሱት ጋዝ ምክንያት አንድ ሰው አየር አጥቶ ህይወቱ ካለፈ በኋላ መሆኑን ነው ቤተሰቡ እና እማኞች የገለጹት።

የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴሩ በበኩሉ ሰውየው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አልነበረም የሞተው ከከተማዋ ርቆ በሚገኝ ቤቱ ነው ብሏል።

ፖሊሶች ጎዳና ላይ በወጡት ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ የተኮሱባቸው ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ድንጋይ ወርውረውባቸዋል።

ይህ ያሁኑ ሁኔታ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ካይስ ሳኢድ በቅርቡ የሰየሟቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መንግሥት በማኅበራዊ እና በመንግሥታዊ አገልግሎቶች ችግር የተነሳ የሚከሰቱ ተቃውሞዎችን እንዴት እንደሚያስተናግድ የሚፈተንበት ይሆናል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG