በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግሪክና ሜቄዶኒያ ጉዳይ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ወጡ


አቴንስ ውስጥ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ
አቴንስ ውስጥ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ

ግሪክና ሜቄዶኒያ ለረጅም ጊዜ ሲያነታርካቸው በኖረው የሜቆዴንያ ስም ጉዳይ መግባባት ላይ ሊደርሱ መቃረባቸውን በመቃወም በብዙ አሥር ሺሕዎች የተቆጠሩ ተቃዋሚዎች አቴንስ ላይ ሰልፍ ወጥተዋል።

ግሪክና ሜቄዶኒያ ለረጅም ጊዜ ሲያነታርካቸው በኖረው የሜቆዴንያ ስም ጉዳይ መግባባት ላይ ሊደርሱ መቃረባቸውን በመቃወም በብዙ አሥር ሺሕዎች የተቆጠሩ ተቃዋሚዎች አቴንስ ላይ ሰልፍ ወጥተዋል።

የግሪክ መንግሥት የአጎራባች ሜቄዶኒያ ስም በመተመለከተ ከሃገሪቱ መንግሥት ጋር እንዳይስማማ ለመጠየቅ የወጣው ሰው ብዛት ፖሊሶች እንደሚሉት አንድ መቶ አርባ ሺህ ይደርሳል። የሰልፉ አደራጆች ግን አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰው ወጥቷል ብለዋል።

ሜቄዶኒያ እኤአ 1991 ከዩጎዝላቪያ ተገንጥላ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ የስሟ ጉዳይ ከግሪክ ጋር ስያናቁራት ቆይቷል። ብዙዎች ግሪኮች በጥንታዊው የታላቁ እስክንድር ንጉሳዊ ግዛት ዋና ጠቅላይ ግዛት የነበረችውን የሜቄዶኒያን ስም ለጎረቤት ሃገር መስጠት የግሪክን ታሪክ ማዋረድ ነው ይላሉ፡፡

ሜቆዴኒያ ይህንኑ ስሟን ይዛ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን የምታደርገውን ግሪክ ስታከላክል ቆይታለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሜቄዶኒያን የቀድሞዋ የዩጎዝላቪያ ሪፐብሊክ ሜቄዶኒያ በሚል ስም ዕውቅና ሰጥቷል።

በሁለቱም ሃገሮች የተቃውሞ ሰልፍ የቀሰቀሰው ግራ ዘመሙ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ለሃያ ሰባት ዓመታት የዘለቀውን ጭቅጭቅ በድርድር ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸው ነው፡፡

በግሪክና ሜቄዶኒያ ጉዳይ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:27 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG