በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህዝባዊ ሰልፍ በዩናይትድ ስቴትስ


የተቃውሞ ሰልፈኞች ከዋይት ኃውስ ቤተ-መንግሥት ፊት ለፊት - ዋሺንግተን ዲሲ
የተቃውሞ ሰልፈኞች ከዋይት ኃውስ ቤተ-መንግሥት ፊት ለፊት - ዋሺንግተን ዲሲ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በሚኒያፖሊስ ሚኔሶታ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ የዘር መድሎን በመቃወም የተቀሰቀሱ ህዝባዊ ቁጣ አዘል ሰልፎች የቀጠሉ ሲሆን፣ የትናንት ማታው ሰልፍ በአብዛኛው ሰላማዊ እንዳነበር ታውቋል።

ኒው ዮርክ ከተማን ባቀፉ በአንዳንድ ቦታዎች፣ የሌሊት ሰዓት እላፊ ገደብ የተደነገገ ቢሆንም፣ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ አዋጆቹን ጥሰው፣ መንገዶች ላይ ወጥተው ነበር።

ኒው ዮርክ ከተማ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አዋጁን ጥሰው በመውጣት፣ ብሩክሊን በተባለው ድልድይ ላይ ለብዙ ሰዓታት ቆይተዋል። ፖሊሶች መውጫ መንገዶቹን ስለዘጉባቸው ነበር ድልድዩ ላይ ለመቆየት የተገደዱት።

በአትላንታ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከሰዓት እላፊው ገደብ በላይ በመንገዶች በመቆየታቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩትን ሰልፈኞች ለመበተን፣ ፖሊሶች እምባ አስመጪ ጋዝ ተኩሰዋል።

አሶሼትድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት በዘገበው መሰረት፣ የተቃውሞ ሰልፎች ባለፈው ሳምንት በሃገርቀፍ ደረጃ ከተነሱበት ጊዜ አንስቶ፣ ቢያንስ 9ሺህ 300 የሚሆኑ ስልፈኞች በፖሊሶች ተይዘዋል።

በዋሺንግተን ዲሲም በመቶዎች የሚቆጠሩ፣ የተቃውሞ ሰልፈኞች ትናንት ማታ ከዋይት ኃውስ ቤተ-መንግሥት ፊት ለፊት ባለው፣ አደባባይ ላይ የሰዓት እላፊ ገደቡን ጥሰው ተቃውሞ ሲያሰሙ አምሽተዋል። በሎሰ አንጀለስ፣ በሚያሚ፣ በኦርላንዶና በሌሎችም በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ አካባቢዎች፣ ተቃውሞዎች ተካሄደዋል።

XS
SM
MD
LG