አዲስ አበባ —
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የበታች ፍርድ ቤት በነ ሃብታሙ አያሌው ላይ የሰጠውን ብይን አቃቤ ሕግ በመቃወም ያቀረበውን ይግባኝ ተቀብሏል፡፡
እሥር ላይ የሚገኙ አምስት ተከሣሾች ሲሆኑ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ሁለቱ ብቻ መሆናቸው ታውቋል፡፡ የቀሩት ያልቀረቡበት ምክንያት አልተገለፀም፡፡
ችሎቱ የሁለቱን ወገኖች የቃል ክርክር ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ለሙሉው የመለስካቸው አምሃ የአዲስ አበባ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡