በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታዋቂ የፓኪስታን ጋዜጠኛ ኬንያ ውስጥ በፖሊስ ተገደለ


ፎቶ ፋይል፦ ጋዜጠኛ አርሻድ ሸሪፍ
ፎቶ ፋይል፦ ጋዜጠኛ አርሻድ ሸሪፍ

በፓኪስታን ታዋቂ ከሆኑ የምርመራ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ኬንያ ውስጥ በጥይት ተመትቶ መሞቱን ፖሊስና ቤተሰቦች አስታወቁ፡፡

የ50 ዓመቱ ጋዜጠኛ አርሻድ ሸሪፍ ትናንት እሁድ ጭንቅላቱን ተመቶ የተገደለው “በተሳሳተ ማንነት” መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ግድያው የተፈጸመው ፖሊስ ዘግቶት በነበረው በማጋዲ ከተማ እና በዋና ከተማው ኖይሮቢ መካከል ባለው አውራ ጎዳና ላይ

ጋዜጠኛው የነበረበትን ተሽከርካሪ ይነዳ የነበረው አሽከርካሪ የመንገድ መሰናክል ጥሶ በመሄዱ በተከፈተ ተኩስ መሆኑን አንድ ታዋቂ የኬንያ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ሟቹ ጋዜጠኛ በትዊተር ላይ ሁለት ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሲሆን በፓኪስታን ታዋቂ በሆነውና the ARY news በተባለው ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተመልካች ያሉት የፖለቲካ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ዝግጅቶችን ያቀርብ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በጋዜጠኛው እና በሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የተሰነዘረውን የግድያ ዛቻና በርካታ የፍርድ ቤት ክሶችን በመሸሽ ከፓኪስታን ተሰዶ የወጣው ባላፈው ነሀሴ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የህግ ባለሙያዎችና የመብት ተሟጋች ቡድኖች የጋዜጠኛውን ሞት አስደንጋጭና እጅግ አሳዛኝ ብለውታል፡፡ የፓኪስታን መንግሥት ኬንያ ውስጥ በተፈጸው ግድያ ዙሪያ ያለውን ዝርዝር ሁኔታ በተሟላ መንገድ እንዲያጣራም ጠይቀዋል፡፡

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍ በትዊተር ባወጡት ጽሁፍ በጋዜጠኛው ሞት በጥልቅ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለፓኪስታን የጸጥታ እና የስለላ መሥሪያ ቤቶች እጅግ ቅርብ ነበር የሚባለው ጋዜጠኛ ሻሪፍ በመንግሥት ባለስልጣናት በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ጥምር መንግሥት አእባላላት በሆኑ ይፈጸማሉ ስለሚባሉ የሙስና አድራጎቶች መረጃ የያዙ ዘገባዎች አዘውትሮ ያቀርብ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ለጸረ ሽብርተኛ ተልዕኮ ከሚሰማሩ የፓኪስታን ወታደሮች ጋርም አብሮ በመጓዝ ይዘግብ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ሆኖም ከቅርብ ወራት ወዲህ የፓኪስታንን የጦር ሰራዊት አመራር እና መንግሥቱን አጥብቆ ይነቅፍ እንደነበር ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG