ዋሺንግተን ዲሲ —
የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ-ብሄር መሆን ብዙዎችን ያስደሰተ ዜና ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል።
የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ለዚያ ከፍ ያለ ሥፍራ መመረጥን የሚያደንቁና በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች አጉልተው የሚያዩት ሴት መሆናቸውን ብቻ ሣይሆን እራሣቸው ወ/ሮ ሣኅለወርቅ እንደባለሙያና እንደመሪም ያሏቸውን የብቃት ማሳያዎችም ጭምር ነው።
ከእንደዚያ ዓይነት ሰዎች መካከል የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ አንዱ ናቸው።
ፕሮፌሰር ብሩክ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ሆነው ነው ያኔ አምባሳደር ሣኅለወርቅን የሚያውቋቸው፤ ዕውቀትና ትውስታቸውን በዚያው ሰሞን ከቪኦኤ ጋር አንስተው ተጨዋውተዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ