ኢትዮጵያውያን የሕይወት ተሞክሮአቸውን፣ በግለ ታሪክ መልክ ለሕዝብ ማስነበብ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በቅርቡ፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም፣ በመኰንን አዳራሽ፣ “ኅብር ሕይዎቴ - ግለ ታሪክ” በሚል ርእስ፣የአድማሳዊው ምሁር ግለ ታሪክ መጽሐፍ ተመርቋል፡፡ በዚኹ የምረቃ መርሐ ግብር፣ ምሁሩ ለአበረከቱት ዘርፈ ብዙ አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ፕር. ባሕሩ ዘውዴ፣ በታሪክ የትምህርት መስክ፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና ተቋማት የሰጡት አገልግሎት፣ አርኣያነት እና ላቂያ እንዳለው ተገልጿል፡፡ የጥናት ሥራቸው ፍሬ የኾኑ ዐያሌ መጻሕፍት እና መጣጥፎች፣ የአቻ ሊቃውንትን አድናቆት አትርፎላቸዋል፡፡
አድማሳዊ ምሁሩ ባሕሩ፣ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን፣ በመላው አፍሪካ፣ በታሪክ ጥናት ከሚጠቀሱ ቀዳሚ ሊቃውንት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ሥራዎቻቸውም፡- በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ፣ ማስተማሪያዎች እንደኾኑላቸው የሚያውቋቸው የሞያው ሊቃውንት መስክረውላቸዋል፡፡
መለስካቸው አምኃ ከፕር. ባሕሩ ዘውዴ ጋራ ያደረገውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም