በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጦር ሰራዊቱን የሚደግፍ ሰልፍ የተቃውሞ ሰልፍ በካርቱም


 የጦር ሰራዊቱን የሚደግፍ ሰልፍ የተቃውሞ ሰልፍ በካርቱም
የጦር ሰራዊቱን የሚደግፍ ሰልፍ የተቃውሞ ሰልፍ በካርቱም

ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ ዛሬ በሺዎች የተቆጠሩ የጦር ሠራዊቱ ወገን የሆኑ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

ቤተ መንግሥቱ ደጃፍ የተሰበሰቡት የተቃውሞ ሰልፈኞች "የረሃብ መንግሥት ይወገድ" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፉ የተጠራው በቀድሞው አምባገነን መሪ ኦመር አል በሽር ላይ ያመጹ ታጣቂ ቡድኖችንም ጭምር ባቀፈው የነጻነት እና የለውጥ ንቅናቄ ጥምረት ውስጥ ከጦር ሠራዊቱ ወገን የሆነ አንጃ መሆኑ ተገልጿል።

ከሰልፉ ቀደም ብሎ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በመንግሥት መስሪያ ቤት ህንጻዎች ዙሪያ ያሉ አጥሮችን በማንሳት ፖሊሶች እና የጸጥታ ጥበቃ አባላት ስራቸው እንዳይገቡ ማድረጋቸው ተመልክቷል።

ትናንት የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ሀገሪቱ ለሁለት ዐመታት በዘለቀው የሽግግር ወቅቷ "ከገጠሙዋት የፖለቲካ ቀውሶች ሁሉ እጅግ የከፋ እና አደገኛ " ሲሉ የገለጹትን ቀውስ ለማክተም የታለመ ዕቅድ ትናንት ይፋ አድርገዋል። "ለቀውሶቹ መፍትሄ ካልተደረገ በስተቀር የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ይጥላል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሲቪላዊውን የአስተዳደሩን ወገን የሚደግፉ ወገኖችም ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG