በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኦሮምያና ትግራይ ክልል የሕግ ታራሚዎች ተፈቱ


prisoners released
prisoners released

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ 7ሺህ 6መቶ አሥራ አንድ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ ፋቷል። 7ሺህ 183 ወንዶች፣ 428 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ 7ሺህ 6መቶ አሥራ አንድ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ ፋቷል። 7ሺህ 183 ወንዶች፣ 428 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

ለሕግ ታሪሚዎቹ ይቅርታ ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ መገርሳ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት በተያዘው ጥረት መሠረት ይህ ይቅጥላል ማለታቸው ተዘግቧል።

መስተዳድሩ ባለፈው መስከረም ወር 2010 ዓ.ም 6ሺህ 655 እስረኞችን መፍታቱም ታውቋል። በታኅሣሥ ወር 2009 ዓ.ም ደግሞ 6,430 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ ተለቀዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ከ2 ሺህ በላይ እስረኞችን በይቅርታ ለመልቀቅ እንደወሰነ፣ የክልሉ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ረደኢ ሀለፎም ለቪኦኤ ገለጹ።

አቶ ረዳኢ፣ እስረኞቹን መፍታት በየዓመቱ ግንቦት ሃያ የሚፈፀም ነው ብለው፣ 54 ሴቶች የሚገኙባቸው 2ሺህ 2መቶ የሕግ ታራሚዎች ባሳዩት መልካም ፀባይ እንዲፈቱ ተወስኗል ሲል፣ ዓለም ፍሥሐ ከመቀሌ ዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG