መቀሌ —
በመቀሌ ማረምያ ቤት ልጆቻችን ሰብዓዊ መብታቸው በጣሰ ተይዘው ይገኛሉ ሲሉ የታራሚዎች ቤተሰብ ገልፀዋል።
በማረምያ ቤቱ ካለፈው ሐምሌ ወር አጋማሽ በማረምያ ቤቱ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ተያይዞ ለብቻቸው በተያዙ ከ70 በላይ ታራሚዎች የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸው ነው ብለዋል።
የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ በዚህ ጉዳይ ተጠይቆ ተራሚዎቹ በቃጠሎ ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸው በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ዝርዝር ማብራርያ አልሰጠበትም ብልዋል። ቅሬታ አቅራቢዎችንና የሚመለከተው አካል ምላሽ ይዘናል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ