በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእሥር ቤቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ


እሥር ቤቶችና የታሣሪዎች ደኅንነት በኢትዮጵያ
እሥር ቤቶችና የታሣሪዎች ደኅንነት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ እሥረኞች የሚያዙበት ሁኔታ የጭካኔ አያያዝ የተደባለቀበት እንደሆነ የሚገልፁ ክሦች ይሰማሉ፤ የወኅኒ ቤቶች አስተዳደር ግን ያስተባብላል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እሥረኞች የሚያዙበት ሁኔታ የጭካኔ አያያዝ የተደባለቀበት እንደሆነ የሚገልፁ ክሦች ይሰማሉ፤ የወኅኒ ቤቶች አስተዳደር ግን ያስተባብላል።

በአዋጅ ቁጥር 1/1987 ነኀሴ 15/1987 ዓ.ም. የወጣውና ዛሬም ሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት ከአንቀፅ 14 አንስቶ በክፍል አንድ ከደነገጋቸው ሰብዓዊ መብቶች ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ አንቀፅ 23 የተደረደሩት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተያዙና በሕግ ጥበቃ ሥር የሚገኙ ሰዎችን የሚመለከቱ ናቸው።

ድንጋጌዎቹ ማንኛውም ሰው የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነትና የነፃነት መብት እንዳለው፣ በሕግ በተደነገገ ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን እንደማያጣ፣ በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት እንዳለው ያረጋግጣሉ።

ሕገመንግሥቱ ኢሰብአዊና የጭካኔ አያያዝን፣ የኃይልና የማስገደድ ምርመራን ይከለክላል።

የተያዙ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጠበቆቻቸው፣ ከሃኪም ጋር የመገናኘት መብት እንዳላቸው ያዝዛል።

ይህንን ሕገመንግሥት መሪዋ አድርጋ እንደምትንቀሳቀስ የምትናገረው ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች አያያዟ ላይ የማነሱባት ክሦችና ውንጀላዎች ከመንደርና ከቀበሌ አንስቶ በብሄራዊና በዓለምአቀፍ መድረኮች ቁጥራቸው ብዙ፣ ሥፍራቸው በአጭር ተነግሮ የማያልቅ ነው።

በየአጋጣሚው ከሚስተዋሉ ጥሰቶች እስከ አደባባይ በሰልፈኞች ላይ የሚፈፀሙ መደዳ ግድያዎች ናቸው ጥፋት እየተባሉ የሚነሱባት።

የመብቶች ረገጣዎች ይካሄዳሉ የሚባሉት በራሱ በመንግሥቱ የፀጥታና የማረሚያ ተቋማት ቁጥጥር ሥር በየፖሊስ ጣቢያውና በየወኅኒ ቤቱ ውስጥ ባሉ የሕግ ታራሚዎች፣ እንዲሁም ጉዳዮቻቸው ገና እየታዩ ባሉ ተመርማሪዎችና ችርት ተመላላሾች ላይም ነው።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፌደራልና የክልሎች እሥር ቤቶችን ሁሉ እንዲጎበኝ ፍቃድ እንደተሰጠው ገልጿል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አንድ ዓመት የፈጀ ፍተሻ በእሥር ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ አካሂዶ ሪፖርቱን በዚህ በጥቅምት መጨረሻ ለተወካዮች ምክር ቤት ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

ፌደራሉ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ደግሞ እሥረኞችን የሚይዘው ሰብዕናቸውን ጠብቆ እንደሆነ አመልክቷል።

የተያያዘው የድምፅ ፋይል ብዙ ወገኖችን ያካተተ ዘገባ ይዟል፤ ያዳምጡት።

የእሥር ቤቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:31:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG