በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መወያየት ተገቢ ነው ብለዋል


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሁለተኛው የትራንስፎርሜሽን ረቂቅ እቅድ ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መወያየት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሁለተኛው የትራንስፎርሜሽን ረቂቅ እቅድ ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መወያየት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን አስታወቁ። ተቃዋሚ ፓረቲዎች ከገዠው ፓርቲ ጋር ባላቸው የፖሊሲ ልዩነቶች ላይ ለመወያየትም መድረኩ ክፍት እንደሆነ ገልጸዋል። መድረክ፣ ሰማያዊ ፓርቲና መኢአድ በስብሰባው አልተገኙም። በውይይቱ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ የፍትህና ዴሚክራስያዊ ሃይሎች ግንባር፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲና አንድነትን ጨምሮ 20 የፖለቲካ ፓርቲዎች በስብሰባው እንደትሳተፉ የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ጠቁሟል።

በቦታው የተገኘው ዘጋብያችን መለስካቸው አመሀ ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል። የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መወያየት ተገቢ ነው ብለዋል /ርዝመት - 6ደ32ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG