በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብር ምንዛሬ ማስተካከያው የዋጋ ንረትን አስከተለ


የአመትበአል ገበያ በልደታ ጉልት
የአመትበአል ገበያ በልደታ ጉልት

የአመት በአሎች መደራረብ የዋጋ ጭማሪውን አባብሶታል

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የብርን የውጭ ምንዛሬ ቀንሷል። የአንድ የአሜሪካ ዶላር በ16.4 ብር እንዲመነዘር ለባንኮች የተላለፈው መመሪያ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል።

ይህንን ተከትሎ ከውጭ አገር የሚገቡ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከስቷል።

ሸማቾች እንደሚናገሩት ሰሞኑን የሸቀጦችና የምርቶች ዋጋ በእጅጉ ጨምረዋል።

ብር ከውጭ አገር የመገበያያ ገንዘቦች ጋር ያለው ዋጋ እንዲወርድ መመሪያው ከተላለፈ በኋላ ሱቆች ከውጭ አገር በሚያስገቧቸው ምርቶች ላይ ተመሳሳይ የሆነ ጭማሪ አድርገዋል።

በአንዳንድ እቃዎች የ20 ከመቶ ጭማሪም ታይቷል።

አዲስ አመት እየቀረበ ነው። ለአንድ ወር የሚዘልቀው የረመዳን ጾምም በመገባደድ ላይ ይገኛል። በዋጋ ደረጃ ደግሞ የሁለቱ በአሎች መደራረብ ፍላጎቱን እንደሚጨምርና ተከትሎ የዋጋ መናር እየታየ መሆኑን ያነጋገርናቸው ሸማቾች ገልጸውልናል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG