በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ክልሉ መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደተከፈተበት ገለፁ


የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

"ህወሃት በአማራ ክልል በተለይ በደቡብ ወሎ ዞን ደሴንና ኮምቦልቻን ለመያዝ ብዙ ኃይል እያንቀሳቀሰ ነው" በማለት "ህዝቡ ወጥቶ እንዲመክት" ሲል የአማራ ክልል መንግሥት ጥሪ አቀርቧል።

አዲሱ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ሥራቸውን ከጀመሩ አንስቶ የመጀመሪያቸው የሆነውን የዛሬውን መግለጫ ሲሰጡ "ወራሪ" ብለው የጠሩት “የትግራይ ኃይል የአማራን ክልል በስፋት ለመውረር ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኃይል ወደ ደቡብ ወሎ እያጓጓዘ ነው” ብለዋል።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይልቃል "ወራሪ" ብለው የጠሩት ኃይል በፈፀመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና የቅርቡን ሳያካትት ወደ 500 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

ሰሞኑን ደግሞ በደቡብ ወሎ ዞን በተለይ ደግሞ ደሴንና ኮምቦልቻን ከተማን ለመያዝ በተከፈተ ጦርነት መጠነ ሰፊ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር ይልቃል አሁን እየደረሰ ነው ያሉት ጥቃት በአማራ በአፋር ክልል ላይ የተሰነዘረ እንደሆነም ጠቁመዋል።

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ክልሉ መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደተከፈተበት ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:42 0:00


XS
SM
MD
LG