በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ብሔራዊ ፕሬስ ክለብ ጠየቀ


ሥልጠና እና የመረጃ ልውውጥን ጨምሮ ለጋዜጠኞች የተለያዩ አገልግሎቶቹን የሚሰጠው የዩናይትድ ስቴትሱ ናሽናል ፕሬስ ክለብ ትናንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ታስረው የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠይቋል።

የተቋሙ ፕሬዚዳንት ጄን ጀድሰን እና የጋዜጠኝነት ሞያ ኢንስቲትዩቱ ፕሬዚዳንት ጊል ክላይን፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ክስ ሳይመሰረትባቸው ታስረው የሚገኙትን የቪዲዮ ጋዜጠኛው አሚር አማን ኪየሮ እና የሞያ ባልደረቦቹ ቶማስ እንግዳ እና ታምራት ነገራን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ መጠየቃቸውን አመልክቷል።

በሀገሪቱ የቀጠለውን ግጭት በተመለከተ ለአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ የሚያጠናቅረው አሚር አማን ኬሮ፤ "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እና የጸረ ሽብር ሕግጋቱን ጥሶ ከኦሮሞ ነጻ አውጪ ጦር አባላት ጋር ቃለ አካሂዷል" በሚል ተወንጅሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ ከአንድ መቶ ቀን በላይ እንዳለፈው የፕሬስ ክለቡ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

"የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የወነጀሉት የጋዜጠኝነት ሥራውን በመስራቱ ነው። ደጋግመን እንደምንናገረው ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም" ሲሉም የብሔራዊ ፕሬስ ክለብ ባለሥልጣናቱ በመግለጫው ላይ ጨምረው አስፍረዋል።

"በማስከተልም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች የዲሞክራሲያቸው መሰረት ጋዜጠኞች ሥራቸውን በመሥራታቸው የማይወነጀሉበት ነጻ ፕሬስ ሲኖር ነው" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG